ሉቃስ 14:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሪያውም፣ ‘ጌታዬ፤ ያዘዝኸው ሁሉ ተፈጽሟል፤ ገና አሁንም ቦታ አለ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩም ‘ጌታ ሆይ! እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፤ ሆኖም ገና ስፍራ አለ፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩም ተመልሶ መጣና ጌታውን ‘ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ፤ ሆኖም ገና ትርፍ ቦታ አለ’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ አገልጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያውም፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፥ ገናም ስፍራ አለ አለው። |
“ባሪያውም ተመልሶ መጥቶ ይህንኑ ለጌታው ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን፣ ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው አውራ ጐዳናዎችና መተላለፊያ መንገዶች ውጣ፤ ድኾችንና አካለ ስንኩሎችን፣ ዐይነ ስውሮችንና ዐንካሶችን ወደዚህ አስገባቸው’ አለው።