ሉቃስ 13:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለከርሞ ካፈራች መልካም ነው፤ አለዚያ ትቈርጣታለህ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደፊትም ብታፈራ፥ መልካም ነው፤ ያለዚያ ግን ትቈርጣታለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመጪው ዓመት ፍሬ ብትሰጥ መልካም ነው፤ አለበለዚያ ግን ትቈረጣለች።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባት ለከርሞ ታፈራ እንደ ሆነ፥ ያለዚያ ግን እንቈርጣታለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፊትም ብታፈራ፥ ደኅና ነው፤ ያለዚያ ግን ትቈርጣታለህ አለው። |