ሉቃስ 13:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምኵራቡ አለቃ ግን፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምኵራብ አለቃው ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን “ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይሆንም፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስን በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ። |
“ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።