ሉቃስ 12:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደቡብ ነፋስም ከደቡብ በኩል ሲነፍስ፣ ‘ቀኑ ሞቃት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ ‘ትኩሳት ይሆናል፥’ ትላላችሁ፤ እንዲሁም ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ነፋስ በስተ ደቡብ በኩል በሚነፍስበት ጊዜ፥ ‘ዛሬ ሙቀት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዜብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆናል፤’ ትላላችሁ እንዲሁም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ፦ ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል። |
‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሓይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋራ እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት።