ሉቃስ 12:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ ይመስላችኋል? አይደለም፤ እላችኋለሁ፤ እኔ የመጣሁት ለመለያየት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በምድር ላይ ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እኔስ ያመጣሁት መለያየትን እንጂ ሰላምን አይደለም እላችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡንም እንዲህ አላቸው፥ “ለምድር ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፤ ሰይፍንና መለያየትን ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። |
ከአሁን ጀምሮ እርስ በርስ የተለያዩ በአንድ ቤተ ሰብ ውስጥ ዐምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሁለቱ በሦስቱ ላይ፣ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።