ሉቃስ 12:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መፍራት የሚገባችሁን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት፤ አዎን፣ እርሱን ፍሩት እላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ እርሱን ፍሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እነግራችኋለሁ፤ ይኸውም ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እግዚአብሔርን ነው፤ አዎ፥ እርሱን ብቻ ፍሩ እላችኋለሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን፤ የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ እናንተስ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ሊጥል ሥልጣን ያለውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላችኋለሁ፤ እርሱን ፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እርሱን ፍሩ። |
የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ ማነው? ክብር ይገባሃልና። ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣ እንደ አንተ ያለ የለም።
ወደ ግብጽም የሄዱት ከባቢሎናውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው።
ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።
“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።
በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታልል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤
በታላቅ ድምፅም፣ “እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሷል፤ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረው ስገዱ” አለ።
ጌታ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ፣ ስምህን የማያከብርስ ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና። የጽድቅ ሥራህ ስለ ተገለጠ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ።”