ሉቃስ 12:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወዳጆቼ ሆይ፤ እላችኋለሁ፣ ሥጋን የሚገድሉትን፣ ከዚያ ወዲያ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተም ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን የሚገድሉትን፥ ከዚያ አልፈው ግን ፈጽሞ ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእናንተ ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን ከመግደል በቀር ሌላ ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተ ለወዳጆች እላችኋለሁ፦ ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሩአቸው፤ ከዚህም የበለጠ ማድረግ የሚችሉት የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ። |
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋራ ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።
ወደ ግብጽም የሄዱት ከባቢሎናውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ እነርሱን ወይም ቃላቸውን አትፍራ፤ ኵርንችትና እሾኽ በዙሪያህ ቢኖሩም፣ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም፣ አንተ በሚሉህ ነገር አትፍራ፤ እነርሱም አያስደንግጡህ።
ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።
ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋራ እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።
ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ። እነሆ፤ ዲያብሎስ ሊፈትናችሁ አንዳንዶቻችሁን ወደ እስር ቤት ይጥላል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።