ሉቃስ 11:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲመጣም ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተመልሶ ሲመጣ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጣም ጊዜ ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። |
“ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሳያገኝም ሲቀር፣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል፤
ከዚያም በኋላ ሄዶ ሌሎች ከርሱ የከፉ ሰባት ክፉ መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆንበታል።”