Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 36:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እራሱን ሸንግሎአልና፥ ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤ መልካም ሥነ ምግባርን ሁሉ መረዳት አቃተው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 36:3
26 Referencias Cruzadas  

አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።


“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”


አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።


ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ።


እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።


ከእነርሱም አንድ የኦሪት ሕግ ዐዋቂ፣ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ አለው፤


እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣ እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”


ምላሳቸውን እንደ እባብ ያሾላሉ፤ ከከንፈራቸውም በታች የእፉኝት መርዝ አለ። ሴላ


ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።


እናንተ በሕዝቡ መካከል ያላችሁ ደነዞች፤ ልብ በሉ፤ እናንተ ሞኞች፤ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?


ክፉዎች በማሕፀን ሳሉ ከመንገድ የወጡ ናቸው፤ ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው።


በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።


ሳኦልም፣ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለ ከበረች፣ ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ በርግጥ የሞኝ ሥራ ሠርቻለሁ፤ እጅግ ሲበዛም ተሳስቻለሁ” አለ።


ሳኦልም በልቡ፣ “ወጥመድ እንድትሆነው፣ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል ዐሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን፣ “እነሆ፤ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።


የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ስለ ራቀ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ክፉ መንፈስ ያሠቃየው ነበር።


ሳሙኤል ግን፣ “ከአንተ ጋራ አልመለስም፤ አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃል፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል” አለው።


የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።


እርሱም በአካሄዱ ሁሉ የአባቱን የአሳን መንገድ ተከተለ፤ ከዚያም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔርም ፊት መልካም የሆነውን አደረገ፤


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ በዐይናቸው አይዞርም።


ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ ጠላትም ያሳድዳቸዋል።


ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios