አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።
ዘሌዋውያን 22:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህናት ትእዛዞቼን በመናቅ በደለኛ እንዳይሆኑና እንዳይሞቱ ይጠብቋቸው፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባረክሱት ጊዜ እንዳይሞቱ ስለ እርሱም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ትዛዝን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህናት ሁሉ እኔ የሰጠኋቸውን የሥርዓት መመሪያዎች ይጠብቁ፤ ይህን ባያደርጉ ግን ለተቀደሱት የትእዛዝ መመሪያዎች ባለመታዘዛቸው በደል ሆኖባቸው ይሞታሉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ ስለ እርስዋም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው።
ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”