ኢያሱ 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ላይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በዐይ ከተማዎች ላይ ያደረገውን ሁሉ ስለ ሰሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገባዖን የሚኖሩ ሰዎች ግን እግዚአብሔር በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ |
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ።
በዚያው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንደ ነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዐምስተኛ ወር፣ የገባዖኑ ሰው የዓዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት፣ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፤
የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን ይዞ እንደ ደመሰሳት፣ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ማድረጉን፣ የገባዖን ሰዎችም ከእስራኤል ጋራ የሰላም ውል አድርገው በአጠገባቸው መኖራቸውን ሰማ።
በዚህም እርሱና ሕዝቡ ደነገጡ፤ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ፣ በስፋቷም ከጋይ የምትበልጥ፣ ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።
በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከተማዪቱንና ንጉሧንም በሰይፍ ስለት መታ፤ አንድም ሰው ሳያስቀር በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፣ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከተማዪቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ፤ አንድም ሰው አላስተረፈም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ ደገመው።
ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ።
ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እዚሁ አጠገባችን መኖራችሁ የታወቀ ሆኖ ሳለ፣ ‘የምንኖረው ከእናንተ በራቀ ስፍራ ነው’ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው?