ኢያሱ 8:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያደፈጡትም ሰዎች እንደዚሁ ከከተማዪቱ ወጥተው መጡባቸው። ስለዚህ እስራኤላውያን በዚያም በዚህም ስለ ከበቧቸው የጋይን ሰዎች ከመካከል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም ሰዎቹን ፈጇቸው፤ አንድ እንኳ የተረፈ ወይም ያመለጠ አልነበረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹም በእነርሱ ላይ ከከተማይቱ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፤ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ከተማይቱም ገብተው የነበሩት እስራኤላውያን ወደ እነርሱ ወርደው የጦርነቱ ተካፋዮች ሆኑ፤ ስለዚህም የዐይን ሰዎች የተወሰኑ እስራኤላውያን በአንድ በኩል፥ ሌሎች ደግሞ በሌላ በኩል ከበዋቸው ስለ ነበረ ወደየትም ለማምለጥ አልቻሉም። ከእነርሱም አንድ እንኳ እንዳያመልጥ ወይም በሕይወት እንዳይኖር ሁሉንም ፈጁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ከከተማ ወጥተው ተቀበሉአቸው፤ በእስራኤል ልጆች ሠራዊት መካከልም አገቡአቸው፤ እኒያ ከወዲያ፥ እኒህም ከወዲህ ሆነው አንድ እንኳን ሳይቀርና ሳያመልጥ ገደሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎቹም በላያቸው ከከተማይቱ ወጡ፥ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፥ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው። |
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጠህና አንተም ድል ባደረግሃቸው ጊዜ፣ ሁሉንም ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፤ አትራራላቸውም።
በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከተማዪቱንና ንጉሧንም በሰይፍ ስለት መታ፤ አንድም ሰው ሳያስቀር በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፣ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጉን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ያደፈጠው ጦር ከተማዪቱን መያዙንና ጢሱ ወደ ላይ መውጣቱን ሲያዩ፣ ወደ ኋላ ተመልሰው በጋይ ሰዎች ላይ አደጋ ጣሉባቸው፤