እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
ኢያሱ 7:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም ከመላው እስራኤል ጋራ ሆኖ፣ የዛራን ልጅ አካንን፣ ብሩን፣ ካባውን፣ የወርቁን ቡችላ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የከብቱን መንጋ፣ አህዮቹንና በጎቹን እንዲሁም ድንኳኑንና የርሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ አስወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ካባውንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ከመላው የእስራኤል ሕዝብ ጋር ዓካንን ይዞ ብሩን፥ ካባውን፥ የወርቅ ምዝምዙን ከዓካን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ጋር ከብቶቹን፥ አህዮቹንና በጎቹን ጭምር፥ ድንኳኑንና የእርሱ ንብረት የሆነውን ሁሉ ሰብስቦ፥ ወደ አኮር ሸለቆ አመጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ልብሱንም፥ ልሳነ ወርቁንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰዳቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ንብረቱንም ሁሉ ወደ ዔሜቃኮር ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ካባውንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው። |
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤
በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብጽ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።
ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል።
የዛራ ልጅ አካን፣ ዕርም የሆነውን ነገር በመውሰድ ኀጢአት ስለ ሠራ፣ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ላይ ቍጣ አልመጣምን? በሠራው ኀጢአት የሞተውም እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ”
እናንተ ግን ዕርም ከሆኑት ነገሮች አንዳች በመውሰድ በራሳችሁ ላይ ጥፋት እንዳታመጡ እጃችሁን ሰብስቡ፤ አለዚያ የእስራኤልን ሰፈር ለጥፋት ትዳርጋላችሁ፤ ክፉ ነገር እንዲደርስበትም ታደርጋላችሁ፤
በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጉን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
እስራኤላውያን ግን ዕርም የሆነውን ነገር ለራሳቸው በመውሰድ በደሉ፤ ይህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው አካን የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ ዕርም ከሆነው ነገር ስለ ወሰደ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።
በአካንም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን ታላቅ የድንጋይ ቍልል ከመሩበት፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቍጣው ተመለሰ። ስለዚህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ያ ስፍራ የአኮር ሸለቆ ተባለ።