La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያ የወጡት ሰዎች ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በጕዞ ላይ ሳሉ የተወለዱት ግን በሙሉ አልተገረዙም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ የተወለዱት ልጆች ሁሉ አልተገረዙም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጀመሪያ ከግብጽ ምድር የወጡት ወንዶች ሁሉ ተገርዘው የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በበረሓው ጒዞ ጊዜ የተወለዱት ወንዶች አልተገረዙም ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፥ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:5
9 Referencias Cruzadas  

‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወድዳለሁ’ የሚለው ቃል ምን ማለት እንደ ሆነ ብታውቁ ኖሮ፣ በንጹሓን ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር።


ያልተገረዙት ሕጉ የሚያዝዘውን የሚፈጽሙ ከሆነ፣ እንደ ተገረዙ አይቈጠሩምን?


መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ ዋናው ነገር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸሙ ነው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።


መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው።


እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ።


ግብጽን ለቅቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና።