ኢያሱ 5:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ጌታ ኢያሱን፦ “የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን “ከባልጩት የተሠራ መቊረጫ አዘጋጅተህ እስራኤላውያንን እንደገና ግረዛቸው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፥ “ከሻፎ ድንጋይ የባልጩት መቍረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ዳግመኛ ግረዛቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፦ የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው አለው። |
ዳሩ ግን አንድ ሰው ይሁዲ የሚሆነው በውስጣዊ ማንነቱ ይሁዲ ሆኖ ሲገኝ ነው። ግዝረትም ግዝረት የሚሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ በመንፈስ የልብ ግዝረት ሲኖር ነው። እንዲህ ያለው ሰው ምስጋናው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ሳይገረዝ በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ፣ የመገረዝን ምልክት ይኸውም የጽድቅን ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙት ጽድቅ ይቈጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው።
አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወድደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህ እግዚአብሔር የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።