ኢያሱ 23:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ ሕዝቦች ጋራ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውን ስም አትጥሩ፤ አትማሉባቸው፤ አታገልግሏቸው፤ አትስገዱላቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር አትቀላቀሉ፤ የአማልክቶቻቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተም መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክቶቻቸውም ስሞች በእናንተ መካከል አይጠሩ፤ አትማሉባቸውም፤ አታምልኳቸውም፤ አትስገዱላቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም፥ |
ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ አንድ ነገር ብቻ አገልጋይህን ይቅር ይበለው፤ ይኸውም ጌታዬ ለመስገድ ወደ ሬሞን ቤተ ጣዖት በሚገባበት ጊዜ ክንዴን ሲደገፍ እኔም እንደ እርሱ በዚያ ብሰግድ፣ በሬሞን ቤተ ጣዖት በመስገዴ እግዚአብሔር አገልጋይህን ይቅር ይበለው።”
“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ተመልሳችሁ የሰጠኋችሁን ሥርዐቶቼንና ትእዛዞቼን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣
አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤
የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤
“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።
“ ‘የምድሪቱን ነዋሪዎች አሳድዳችሁ ሳታስወጧቸው ብትቀሩ ግን፣ እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ሰዎች ለዐይናችሁ ስንጥር፣ ለጐናችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል፤ በምትኖሩበትም ምድር ችግር ይፈጥሩባችኋል።