ኢያሱ 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኢያሪኮም ንጉሥ፣ “እነሆ፤ ምድሪቱን ሊሰልሉ ጥቂት እስራኤላውያን በሌሊት ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አገሪቱን ለመሰለል ከእስራኤላውያን መካከል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ለኢያሪኮ ንጉሥ ተነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኢያሪኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእስራኤል ልጆች ሰላዮች ሀገራችንን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ። |
የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።
ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።
የኢያሪኮም ንጉሥ፣ “ወደ አንቺ መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡት ሰዎች ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ስለ ሆነ፣ እንድታስወጪአቸው” የሚል መልእክት ወደ ረዓብ ላከ።
ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ ዐምስት ኀያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፣ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው። መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ።