ኢያሱ 19:46 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሜያ-ርቆንን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆንን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሜያርቆን፥ ራቆንና እንዲሁም በኢዮጴ ዙሪያ ያለውን ግዛት ጭምር ያጠቃልላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕር በኩል በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያራቆን። |
እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።
በኢዮጴ ጣቢታ የተባለች አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጓሜ ዶርቃ ማለት ነው። እርሷም ዘወትር በትጋት በጎ ነገር እያደረገችና ድኾችን እየረዳች ትኖር ነበር።
ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች፣ ደቀ መዛሙርትም ጴጥሮስ በልዳ መሆኑን በሰሙ ጊዜ ሁለት ሰዎች ልከው፣ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና!” ሲሉ ለመኑት።
ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።