ኢያሱ 18:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፊርዓሞናይ፣ ዖፍኒ እንዲሁም ጌባዕ ናቸው፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፥ ጋባ፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፋርዐሞናይ፥ ዖፍኒና፥ ጌባዕ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ትናንሽ ከተሞችንም መንደሮችንም ይጨምራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ንጉሥ አሳ አንድም ሰው እንዳይቀር በይሁዳ ሁሉ ዐዋጅ አስነገረ፤ ከዚያም ሕዝቡ ባኦስ በራማ ሲሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት አጋዘ፤ በእነርሱም ንጉሡ አሳ የብንያምን ጌባዕና ምጽጳን ሠራበት።
ኢዮስያስ የቤተ ጣዖት ካህናትን ሁሉ ከይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም አወጣቸው፤ ከጌባዕ ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ ካህናቱ ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎችን አረከሰ። ከከተማዪቱ በር በስተግራ በኩል፣ በከተማዪቱ ገዥ በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን ማምለኪያ ስፍራዎች አፈረሰ።
ዮናታን ጌባዕ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ።