ኢያሱ 13:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው እርሱ ራሱ ርስታቸው ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንደ ነገራቸው እንዲሁ ርስታቸው እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ ሲሆን፥ ሙሴ ለሌዊ ነገድ የሚሰጥ የርስት ድርሻ አልመደበም፤ የእነርሱ ርስት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ድርሻቸውን የሚያገኙት ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው መሥዋዕት መሆኑን ነግሮአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳላቸው ርስታቸው እርሱ ነው። |
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “ከምድራቸው የምትካፈለው ርስት፣ ከእነርሱም የምታገኘው ድርሻ የለህም፤ በእስራኤላውያን መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።
ሌዋውያኑ ግን ለእግዚአብሔር የሚሰጡት የክህነት አገልግሎት ርስታቸው ስለ ሆነ በእናንተ መካከል ድርሻ አይኖራቸውም። ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምሥራቅ ዮርዳኖስ የሰጣቸውን ርስት ቀደም አድርገው ወስደዋል።”