ኢያሱ 12:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቴርሳ ንጉሥ፣ አንድ እነዚህ በድምሩ ሠላሳ አንድ ነገሥታት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲርጻ ሲሆኑ፥ ነገሥታቱም በሙሉ ሠላሳ አንድ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ነገሥት ሁሉ ሃያ ዘጠኝናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው። |
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት፣ ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ፤ ከዚህም ውስጥ ስድስቱን ዓመት የገዛው በቴርሳ ሆኖ ነው።
በምድሪቱ ወንዶች ልጆቻቸው ገቡባት፤ ወረሷትም። በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን በፊታቸው አንበረከክህ፤ ያሻቸውን ያደርጉባቸው ዘንድ ከነዓናውያንን ከንጉሦቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋራ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
ነገሥታታቸውን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ። እስክትደመስሳቸው ድረስ አንተን መቋቋም የሚችል አንድም ሰው የለም።