ኢያሱ 11:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱና ሰራዊቱ ሁሉ በድንገት ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ወጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከተዋጊዎቹ ሁሉ ጋር በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጣባቸው፥ በእነርሱም ላይ ጥቃት ፈጸመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያሱና መላ ሠራዊቱ ዘምተው በሜሮም ድንገተኛ አደጋ ጣሉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱና ተዋጊዎች ሕዝብም ሁሉ በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጡባቸው፤ በተራራማውም ቦታ ወደቁባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከሰልፈኞቹ ሁሉ ጋር በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጣባቸው፥ ወደቀባቸውም። |
እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ስለ ሰጣቸው ድል አደረጓቸው። በታላቂቱ ሲዶና መንገድ መጨረሻ እስከ ማስሮን፣ በስተ ምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዷቸው፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።