ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።
ኢያሱ 11:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፥ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ አለው። |
ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።
ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነርሱ በጺጽ መተላለፊያ ሽቅብ ይወጣሉ፣ እናንተም በይሩኤል ምድረ በዳ ውስጥ በሸለቆው መጨረሻ ላይ ታገኟቸዋላችሁ።
ደግሞም ‘አይሆንም፣ በፈረስ እንሸሻለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ ትሸሻላችሁ! ደግሞም፣ ‘በፈጣን ፈረስ እናመልጣለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ አሳዳጆቻችሁም ፈጣን ይሆናሉ።
ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብጽ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!
“ ‘ከዚያም በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ወጥተው የጦር መሣሪያውን፣ ትልልቁንና ትንንሹን ጋሻ፣ ቀስቱን፣ ፍላጻውን፣ የጦር ዱላውንና ጦሩን ሰብስበው ማገዶ በማድረግ ያነድዱታል፤ ሰባት ዓመት ይማግዱታል።
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤ ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤ የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤ የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።”
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ማጥፋት አለብህ፤ አትዘንላቸው፤ ወጥመድ ስለሚሆኑብህም አማልክታቸውን አታምልክ።
የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፣ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደ ገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ።