ኢያሱ 11:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ሰራዊታቸውን ሁሉ እጅግ ብዙ ከሆኑ ፈረሶችና ሠረገሎች ጋራ ይዘው ወጡ፤ የሰራዊቱም ብዛት በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ፥ በቍጥር ም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ከሚሆን ብዙ ሕዝብ፥ እጅግም ከሚበዙ ፈረሶችና ሰረገሎች ጋር በመሆን ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከነወታደሮቻቸው ስለ መጡ፥ የሠራዊቱ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ሆነ፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ፥ ከእነርሱም ጋር ሠራዊቶቻቸው ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም እጅግ ብዙዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ከእጅግም ብዙ ፈረሰኞና ሠረገሎች ጋር ወጡ፥ በባሕር ዳርም እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበረ። |
“እንግዲህ እኔ የምመክርህ ይህ ነው፤ ቍጥሩ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛው፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ ይሰብሰብና አንተው ራስህ ወደ ጦርነቱ ምራው፤
ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።
ፍልስጥኤማውያን ሦስት ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።