ኢያሱ 11:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር፣ ከእስራኤላውያን ጋራ የሰላም ውል ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም፤ ሁሉንም የያዙት በጦርነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፤ ሁሉንም በጦርነት ድል አድርገው ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ስምምነት አድርጋ በሰላም የኖረች አገር ከሒዋውያን ወገን የገባዖን ኑዋሪዎች በቀር ሌላ አልነበረም፤ ሌሎቹ በሙሉ በጦርነት ድል ሆነው የተያዙ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዎናውያን በቀር፤ እስራኤል ያልያዙት ከተማ አልነበረም፥ ሁሉን በጦርነት ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፥ ሁሉን በሰልፍ ያዙ። |
እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።