ኢያሱ 10:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት ያዟት፤ በሰይፍም ስለት አጠፏት፤ በለኪሶ እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው ደመሰሷቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ያዙአት፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፤ በለኪሶም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርሷ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በዚያ ቀን ፈጽሞ አጠፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑም ዕለት ከተማይቱን ያዙ፤ በሰይፍ መቱአት፤ ልክ በላኪሽ እንዳደረጉት ዐይነት ያገኙትን ሰው ሁሉ ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በእስርኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፤ በዚያም ቀን ያዙአት፤ በሰይፍም ስለት መቱአት፤ በላኪስም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርስዋ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ያዙአት፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ በለኪሶም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርስዋ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በዚያ ቀን ፈጽሞ አጠፋ። |
በዚህ ሁሉ ግን ከእነርሱ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን በማፍረስ፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ፈጽሜ እስካጠፋቸው ድረስ አልተዋቸውም፤ አልጸየፋቸውምም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ።
ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ።