ኢያሱ 10:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም፤ “ዋሻውን ከፍታችሁ እነዚያን ዐምስቱን ነገሥታት አውጥታችሁ አምጡልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢያሱ፦ “የዋሻውን በር ከፍታችሁ በማውጣት እነዚያን አምስት ነገሥታት ወደ እኔ አምጡ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፤ እነዚያንም አምስት ነገሥት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም፦ የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው አለ። |
እነርሱም ዐምስቱን ነገሥታት ማለትም የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፣ የኬብሮንን ንጉሥ፣ የያርሙትን ንጉሥ፣ የለኪሶን ንጉሥ የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት።
ከዚያም ሳሙኤል፣ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግንም በሰንሰለት ተይዞ፣ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን?” በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።