ኢያሱ 10:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ ጠባቂ ሰዎችንም በዚያ አቁሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወደ ዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ፥ እንዲጠብቋቸው ሰዎችን በዚያ አኑሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም እንዲህ ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ “ታላላቅ ድንጋዮች አንከባላችሁ የዋሻውን በር ዝጉ፤ በዚያም ዘብ ጠባቂ አቁሙበት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም እንዲህ አለ፥ “ወደ ዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ፥ ይጠብቋቸው ዘንድ ሰዎችን በዚያ አኑሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ወደ ዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ፥ ይጠብቁአቸው ዘንድ ሰዎችን በዚያ አኑሩ፥ |
ይህ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ፣ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ ወደ ቤቱም ገብቶ፣ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያሳርፍ፣ እባብ እንደሚነድፈው ነው።
ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ ጕልላቶቹን ምታ፤ በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤ የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።
ጠላቶቻችሁን አሳድዷቸው እንጂ ችላ አትበሉ፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም አደጋ ጣሉባቸው፤ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሏቸው፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና።”