እንዲሁም የናሜሲን ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ቅባው፤ ደግሞም ነቢይ ሆኖ በእግርህ እንዲተካ የአቤልምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው።
ኢያሱ 1:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ የጌታ ባርያ ሙሴ ከሞተ በኋላ ጌታ የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ፥ የሙሴ ረዳት የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አነጋገረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
እንዲሁም የናሜሲን ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ቅባው፤ ደግሞም ነቢይ ሆኖ በእግርህ እንዲተካ የአቤልምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው።
ኢዮሣፍጥ ግን፣ “በርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን ለመጠየቅ እንድንችል፣ የእግዚአብሔር ነቢይ እዚህ የለምን?” በማለት ጠየቀ። ከእስራኤል ንጉሥ የጦር አለቆችም አንዱ፣ “ቀድሞ የኤልያስን እጅ ያስታጥብ የነበረው፤ የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ በዚህ አለ” ብሎ መለሰለት።
ከምርኮ የተመለሰውም ማኅበር ሁሉ ዳሱን ሠርቶ ተቀመጠ። ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ጊዜ ድረስ እስራኤላውያን እንደዚያ አድርገው በዓሉን አክብረው አያውቁም፤ ደስታቸውም ታላቅ ነበር።
አባቶቻችንም ድንኳኗን ከተቀበሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ ይዘዋት ገቡ፤ እስከ ዳዊትም ዘመን ድረስ በምድሪቱ ተቀመጠች፤
እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ፣ “በርታ፤ ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና፤ እኔም ከአንተ ጋራ እሆናለሁ” በማለት ትእዛዝ ሰጠው።
አምላክህ እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ምድራቸውን ትወርሳለህ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፣ ኢያሱም አንተን ቀድሞ ይሻገራል።
ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ።
የእግዚአብሔርን ምርጦች እምነትና ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት የሚመራውን የእውነት ዕውቀት ለማሳደግ የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፤
ይህም፣ እግዚአብሔር እስኪያሳርፋቸውና ለእናንተም እንዳደረገው ሁሉ፣ እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተም ተመልሳችሁ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣችሁን፣ በፀሓይ መውጫ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ምድር ትወርሳላችሁ።”
“እነሆ፤ ባሪያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሡ፤ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ።
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።