ኢያሱ 1:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ይህም፣ እግዚአብሔር እስኪያሳርፋቸውና ለእናንተም እንዳደረገው ሁሉ፣ እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተም ተመልሳችሁ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣችሁን፣ በፀሓይ መውጫ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ምድር ትወርሳላችሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ጌታ እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ የጌታ ባርያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱዋታላችሁም።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ እንደ ሰጠው ለወንድሞቻችሁም ዕረፍትን እስኪሰጥና እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ርስት እስኪያገኙ አብራችሁ ዝመቱ። ከዚያ በኋላ ተመልሳችሁ መጥታችሁ፥ በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ማዶ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሰጣችሁ በገዛ ምድራችሁ ትቀመጣላችሁ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 አምላካችን እግዚአብሔር እንደ እናንተ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችን እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ ከእናንተ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በፀሐይ መውጫ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትገባላችሁ፤ ትወርሱአትማላችሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱአትማላችሁ። Ver Capítulo |