እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው።
ዮሐንስ 9:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን። |
እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው።
አሁንም ሚስቱን ለሰውየው መልስለት፤ ነቢይ ነውና ይጸልይልሃል፤ አንተም ትድናለህ፤ ባትመልስለት ግን አንተም ሆንህ የአንተ የሆነ ሁሉ እንደምትሞቱ ዕወቅ።”
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ስለ ራሳችሁ አቅርቡ። እንደ አሳፋሪ ተግባራችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር አልተናገራችሁምና።”
ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር።
ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤ እርሱም መለሰላቸው።
እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል። “የጭቈና ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣
ቢጾሙም ጩኸታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ቢያቀርቡም አልቀበላቸውም፤ ነገር ግን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር አጠፋቸዋለሁ።”
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።