ዮሐንስ 8:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትንም ታውቋታላችሁ፤ እውነትም አርነት ታወጣችኋለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” አላቸው። |
ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ።
እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ አጥብቀን እንከተለው፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ የሚሰማውን ብቻ ይናገራል፤ እንዲሁም ወደ ፊት ስለሚሆነው ይነግራችኋል፤
አሁን ግን ከኀጢአት ነጻ ወጥታችሁ የእግዚአብሔር ባሮች ሆናችኋል፤ የምትሰበስቡትም ፍሬ ወደ ቅድስና ያመራል፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።
ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።