ሹሙም፣ “ጌታዬ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ድረስልኝ” አለው።
ሹሙም “ጌታ ሆይ! ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ፤” አለው።
ሹሙም “ጌታ ሆይ! ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ቶሎ ውረድ” አለው።
ያም የንጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይሞት ፈጥነህ ውረድ” አለው።
ሹሙም፦ ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ አለው።
እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ ጌታ ግን ያስብልኛል። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬም ነህና፤ አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ።
“ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና ድና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው።
ኢየሱስም፣ “መቼውንም እናንተ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን ካላያችሁ አታምኑም” አለው።
ኢየሱስም፣ “ልጅህ በሕይወት ይኖራልና ሂድ” አለው። ሰውየውም ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ፤