ዮሐንስ 3:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው፤ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው፥ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነ ምድራዊ ነው፤ የምድርንም ነገር ይናገራል፤ ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከላይ የመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የተገኘውም ምድራዊ ነው፤ የምድሩንም ይናገራል፤ ከሰማይ የመጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። |
ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ።
ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”
አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው! አሜን።