ዮሐንስ 3:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ለመጠመቅ ይመጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን፥ በዚያ ብዙ ውሃ ነበርና፥ ያጠምቅ ነበር፤ እየመጡም ይጠመቁ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜ ዮሐንስም ብዙ ውሃ ስለ ነበረበት በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም እየመጡ ይጠመቁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሐንስም በዮርዳኖስ ማዶ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን ያጠምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና፤ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ያጠምቃቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥ |
ከሰማይ እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁት ድምፅ በገና ደርዳሪዎች እንደሚደረድሩት ዐይነት ነበረ።
ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና።
ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።