በኢየሩሳሌም በዓላት ላይ እንደሚገኘው የመሥዋዕት በግ መንጋ አበዛዋለሁ። እነሆ! ፈራርሰው የነበሩት ከተሞች የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
ዮሐንስ 2:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤተ መቅደስ ውስጥ ከብቶችን፣ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡ እንዲሁም ተቀምጠው የገንዘብ ምንዛሪ የሚያከናውኑ ሰዎች አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና እርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡትንና ገንዘብ ለዋጮችን ተቀምጠው ሲገበያዩ አገኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፥ ርግቦችንም የሚሸጡትን፥ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደስም በሬዎችንም በጎችን ግንቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ |
በኢየሩሳሌም በዓላት ላይ እንደሚገኘው የመሥዋዕት በግ መንጋ አበዛዋለሁ። እነሆ! ፈራርሰው የነበሩት ከተሞች የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤
ሲያስተምራቸውም፣ “ ‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት!’” አላቸው።