La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 11:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ ጌታን ሽቱ ቀብታ እግሮቹን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህች ማርያም የጌታን እግር ሽቶ የቀባችውና በጠጒርዋ ያበሰችው ናት፤ የታመመውም አልዓዛር የእርስዋ ወንድም ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 11:2
11 Referencias Cruzadas  

እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሠራ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፣ ብልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት።


“ይመጣል የተባለልህ አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ? በሉት” ብሎ ወደ ጌታ ላካቸው።


ማርታም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተ ነበር።


እኅትማማቾቹም፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትወድደው ሰው ታምሟል” ብለው መልእክት ላኩበት።


ማርያምም ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቦታ ደርሳ እንዳየችው፣ እግሩ ላይ ተደፍታ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው።


ማርያምም ዋጋው ውድ የሆነ፣ ግማሽ ሊትር ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ አምጥታ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ እግሮቹንም በጠጕሯ አበሰች፤ ቤቱንም የሽቱው መዐዛ ሞላው።


እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና።


እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል።