ኢዩኤል 3:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ጦረኖች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህን ለአሕዛብ ሁሉ ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ጀግኖችን ቀስቅሱ፤ ጦረኞቻችሁ ሁሉ ተሰብስበው ለጦርነት ይሰለፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህን በአሕዛብ መካከል ዐውጁ፤ ለሰልፍ ተዘጋጁ፤ ኀያላንን አስነሡ፤ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ፤ ይውጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለሰልፍ ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም። |
“ሕዝቦች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ሩቅ ባሉ የባሕር ጠረፎችም፣ ‘እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል’ ብላችሁ ዐውጁ።
“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’
“ፍላጾችን ሳሉ፤ ጋሻዎችን አዘጋጁ፤ የእግዚአብሔር ሐሳብ ባቢሎንን ለማጥፋት ስለ ሆነ፣ የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቷል፤ እግዚአብሔር ይበቀላል፤ ስለ ቤተ መቅደሱ ይበቀላል።
“በምድር ሁሉ ላይ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ! በሕዝቦች መካከል መለከትን ንፉ! ሕዝቦችን ለጦርነት በርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትን፣ የሚኒንና የአስከናዝን መንግሥታት፣ ጠርታችሁ በርሷ ሰብስቧቸው፤ የጦር አዝማች ሹሙባት፤ ፈረሶችንም እንደ አንበጣ መንጋ ስደዱባት።
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቀደመው ዘመን በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገርሁለት ያ ሰው አንተ አይደለህምን? በዚያ ወቅት አንተን በእነርሱ ላይ እንደማመጣባቸው ለብዙ ዓመታት ትንቢት ተናገሩ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቤን የሚያስቱ ነቢያት፣ ሰው ሲያበላቸው፣ ‘ሰላም አለ’ ይላሉ፤ ሳያበላቸው ሲቀር ግን፣ ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።