ሰዎቹንም ሁሉ እያንዳንዱ መሣሪያውን በእጁ ይዞ ከቤተ መቅደሱ ደቡብ አንሥቶ እስከ ሰሜን ድረስ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።
ኢዩኤል 2:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱ ከሌላው ርቆ አይቆምም፤ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ይሮጣሉ፤ በመሣሪያቸው ላይ ይወድቃሉ፤ እነርሱም አይጠፉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም። |
ሰዎቹንም ሁሉ እያንዳንዱ መሣሪያውን በእጁ ይዞ ከቤተ መቅደሱ ደቡብ አንሥቶ እስከ ሰሜን ድረስ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።
ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ።
እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ፣ ሰዎቼም ሆኑ ከእኔ ጋራ ያሉት ጠባቂዎች ልብሳችንን አላወለቅንም፤ ለውሃ እንኳ በምንሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደ ያዘ ነበር።