ኢዩኤል 1:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ቦታዬን ባድማ አደረገው፤ የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስኪታዩ ድረስ፣ ቅርፊታቸውን ልጦ፣ ወዲያ ጣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ተክሎቼን ሁሉ አጠፋ፤ የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስከሚታዩ ድረስ፥ ቅርፊቱን ልጦ ጣለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፤ በለሴንም ሰበረው፤ ተመለከተውም፥ ጣለውም፤ ቅርንጫፎቹም ነጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ። |
እነርሱም ግብጽን በሙሉ ወረሩ፤ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ሆነው የሀገሪቱን ዳር ድንበር ሁሉ አለበሱ። እንዲህ ያለ የአንበጣ መዓት ከዚህ ቀደም አልነበረም፤ ወደ ፊትም ደግሞ አይኖርም።
ምድሩ ሁሉ ጠቍሮ እስኪጨልም ድረስ አለበሱት። ከበረዶ የተረፈውን፣ በመስክ ላይ የበቀለውንና በዛፍ ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠርገው በሉ። በግብጽ ምድር ሁሉ በዛፍ ላይ ወይም በተክል ላይ አንዳች ቅጠል አልተረፈም ነበር።
“ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”
“የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣
ስለ እናንተ ተባዩን እገሥጻለሁ፤ አዝመራችሁን አይበላም፤ ዕርሻ ላይ ያለ የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።