ኢዩኤል 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀያልና ቍጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ፣ ምድሬን ወሯታልና፤ ጥርሱ እንደ አንበሳ ጥርስ፣ መንጋጋውም እንደ እንስት አንበሳ መንጋጋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቍጥር ም የሌለው ብርቱ ሕዝብ በምድሬ ላይ ወጥቶአልና፥ ጥርሳቸው እንደ አንበሳ ጥርስ፥ መንጋጋቸውም እንደ እንስቲቱ አንበሳ መንጋጋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስፍር ቊጥር የሌለው የአንበጣ መንጋ፥ እንደ ወራሪ ጦር በምድሬ ላይ መጥቶአል፤ ጥርሱ እንደ አንበሳ ጥርስ ነው፤ መንጋጋውም እንደ ሴት አንበሳ መንጋጋ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጥርም የሌለው ብርቱ ሕዝብ በምድሬ ላይ ወጥቶአልና፤ ጥርሳቸው እንደ አንበሳ ጥርስ፥ ክንዳቸውም እንደ አንበሳ ደቦል ክንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጥርም የሌለው ብርቱ ሕዝብ በምድሬ ላይ ወጥቶአልና፥ ጥርሳቸው እንደ አንበሳ ጥርስ፥ መንጋጋቸውም እንደ እንስቲቱ አንበሳ መንጋጋ ነው። |
እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”
“በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣ እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።