ኢዩኤል 1:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚበላ ምግብ፣ ከዐይናችን ፊት፣ ደስታና ተድላ፣ ከአምላካችን ቤት አልተቋረጠብንምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይናችን እያየ አይደለምን ከፊታችን ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እህል ከዐይናችን ደስታና እልልታ ከአምላካችን ቤተ መቅደስ፥ ፈጽሞ ጠፍቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዐይኖቻችሁ ፊት ምግብ፥ ከአምላካችሁም ቤት ደስታና ሐሤት ጠፍቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዓይናችን ፊት ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋ አይደለምን? |
ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።