ኤርምያስ 8:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መከሩ አልፎአል፥ በጋው ተፈጽሟል፥ እኛም አልዳንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “እነሆ የመከር ወራት አለፈ፤ በጋውም ተፈጸመ፤ እኛ ግን አልዳንም!” በማለት ይጮኻሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከሩ አልፎአል፤ በጋውም ዐልቋል፤ እኛም አልዳንንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም። |
እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ ከሩቅ ምድር ስማ፤ “እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ንጉሧስ በዚያ አይኖርምን?” “በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣ እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”
የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደ ሆናችሁና ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።