ኤርምያስ 52:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው። ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ የእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፥ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። |
በአንተ ደስ ተሰኝቶ በእስራኤል ዙፋን ላይ ያስቀመጠህ እግዚአብሔር አምላክህ ቡሩክ ይሁን፤ እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅሩም እስራኤልን ከመውደዱ የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን አንተን ንጉሥ አደረገህ።”
እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
እንደዚሁም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ዐንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ እንጂ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም።
ስለዚህ በአባቶችህ ቤተ መዛግብት ምርመራ ይደረግ፤ በእነዚህ መዛግብት ውስጥ ይህች ከተማ ዐመፀኛ ከተማ እንደ ሆነች፣ ነገሥታትንና አውራጃዎችን የጐዳችና ከጥንት ጀምሮ የዐመፅ ጐሬ ስለ መሆኗ ማስረጃ ታገኛለህ፤ እንግዲህ ከተማዪቱ የተደመሰሰችው በዚህ ምክንያት ነው።