ኤርምያስ 5:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፎች እንደ ሞሉት ጐጆ፣ ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ እንደሞላበት የወፍ ቀፎ፥ እንዲሁ ቤቶቻቸው በሽንገላ ተሞልቶአል፤ ስለዚህም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኝ ወፎችን ይዞ በወፎች ጎጆ እንደሚያሰፍር፥ እነርሱም ቤታቸውን ከብዝበዛ ባገኙት ሀብት ይሞላሉ፤ ብርቱዎችና ሀብታሞች የሆኑትም ስለዚህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ በዚህም ከብረዋል ባለጸጎችም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፥ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። |
እግዚአብሔር፣ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋራ እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?
ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።
“ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣ እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።
ከመከራው መገላገልን በመሻት፣ በማሮት የሚኖሩ በሥቃይ ይወራጫሉ፤ እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷልና።
እርሱም በብርቱ ድምፅ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ፣ የርኩስና የአስጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች።