ኤርምያስ 5:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል። ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሏችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደላችሁ በረከትን አሳጣችሁ፤ የኃጢአታችሁም ብዛት መልካም ነገር እንዳታገኙ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደላችሁም እነዚህን አስቀርታለች፤ ኀጢአታችሁም መልካምን ነገር ከእናንተ አርቃለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።
የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ቅጣትሽ ያበቃል፤ እርሱም የስደትሽን ዘመን አያራዝምም፤ ነገር ግን አንቺ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፤ ኀጢአትሽን ይቀጣል፤ ክፋትሽንም ይፋ ያወጣል።