ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
ኤርምያስ 48:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዲቦን፣ በናባውና በቤትዲብላታይም ላይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዲቦን፥ በናባው፥ በቤት ዲብላታይም ላይ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዲቦን፥ በናባው፥ በቤትዲብላታይም ላይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዲቦን፥ በናባው፥ በቤት ዲብላታይም ላይ፥ |
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።
“ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።
እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ የሚኖሩበትንም ስፍራ ከምድረ በዳው እስከ ዴብላታ ድረስ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”