ኤርምያስ 41:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ግብጽም የሄዱት ከባቢሎናውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን በመፍራታቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና። |
ነገር ግን በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዝርያ የነበረው የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ዐሥር ሰዎች ይዞ መጥቶ ጎዶልያስንና በምጽጳ ዐብረውት የነበሩትን የይሁዳን ሰዎችና ባቢሎናውያንን ገደለ።
“እኔን የዋሸሽኝ፤ ማንን ፈርተሽ፣ ማንንስ ሠግተሽ ነው? እኔን ያላስታወስሽው፣ ይህንም በልብሽ ያላኖርሽው፣ እኔን ያልፈራሽው፣ ዝም ስላልሁ አይደለምን?
ኤርምያስ ገና መልስ ሳይሰጥ ናቡዘረዳን በመቀጠል፣ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፤ ከርሱም ጋራ በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ፤ ወይም ወደ ቀናህ ስፍራ ሂድ” አለው። የዘበኞቹ አዛዥ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው፤
አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር፤