ኤርምያስ 16:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ያበጃሉን? ያደርጉ ይሆናል፤ እንዲህ ዐይነቶቹ ግን አማልክት አይደሉም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ሰው አማልክት ያልሆኑትን ለራሱ አማልክት አድርጎ ይሠራልን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ሰው የራሱን አማልክት መሥራት ይችላልን? አዎ፥ ግን እውነተኛ አምላክነት የላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ሰው አማልክት ያልሆኑትን ለራሱ አማልክትን አድርጎ ይሠራልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ሰው አማልክት ያልሆኑትን ለራሱ አማልክትን አድርጎ ይሠራልን? |
“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።
ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የእስያ አውራጃ የሚገኘውን በርካታ ሕዝብ እያሳመነ እንዳሳታቸው ይኸው የምታዩትና የምትሰሙት ነገር ነው፤ በሰው እጅ የተሠሩ አማልክት በፍጹም አማልክት እንዳልሆኑ ይናገራልና።