ኤርምያስ 15:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕመሜ የማይድነው፥ ቊስሌስ የማይጠገነውና የማይፈወሰው ለምንድን ነው? በበጋ ወራት እንደሚደርቅ ጅረት ተስፋ ታስቈርጠኛለህን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን? |
ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።
መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤ እነርሱ ወደ ውሃ ጕድጓዶች ይወርዳሉ፤ ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ ራሳቸውን ተከናንበው፣ ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።